Got a TV Licence?

You need one to watch live TV on any channel or device, and BBC programmes on iPlayer. It’s the law.

Find out more
I don’t have a TV Licence.

ቀጥታ ዘገባ

የተጠቀሱት ሰዓቶቸ የዩናይትድ ኪንግደም ናቸዉ

  1. ኮሮናቫይረስ ምስል

    ከቻይናዋ ሁቤይ ግዛት ተነስቶ ሰው ከማይኖርበት አንታርክቲክ ውጪ ሁሉንም የዓለማችንን አህጉራትን ያዳረሰው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአሁኑ ወቅት የምድራችን ዋነኛ የጤና ስጋት ነው። ኮቪድ-19 በመባል የሚታወቀው ይህ ወረርሽኝ የመተንፈሻ አካልን የሚያጠቃ ሲሆን፤ መጀመሪያ ትኩሳት ቀጥሎም ደረቅ ሳል ከሳምንት በኋላ ደግሞ የትንፋሽ ማጠርን ያስከትላል። እስካሁን በቫይረሱ ከ186 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የተያዙ ሲሆን ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።

    ተጨማሪ ያንብቡ
    next
  2. የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ

    የደቡበ አፍሪካ ፕሬዚዳንት የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ያወጣቻቸውን መመሪያዎች ለማላላት ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን ባስታወቁበት እለትም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ጣሪያው ላይ ደርሷል ብለዋል።

    ተጨማሪ ያንብቡ
    next
  3. ደቡብ ኮሪያ አዲሱ ዙር ወረርሽኝ ከሃይማኖት መሪ ጋር የተያያዘ ነው አለች

    ደቡብ ኮሪያ

    የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት በመግታት ምስጋና ከተቸራቸው መካከል አንዷ ደቡብ ኮሪያ ናት።

    በአሁኑ ወቅት ግን በባለፉት አምስት ወራት ውስጥ ከታየው በበለጠ በዚህ ሳምንት አዳዲስ ህሙማንን መዝግባለች።

    ባለስልጣናቱም አዲሱ ዙር ወረርሽኝ መመሪያዎቹን ከጣሰ የሃይማኖት መሪ ጋር አያይዘውታል። በዚህ ሳምንትም 279 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተጠቁሟል።

    አብዛኛዎቹም ህሙማን የተገኙት በመዲናዋ ሴዑልና አካባቢዋ ነው ተብሏል። ሳራጅ ጄል የተባለው ቤተ ክርስቲያን ቄስና ኃላፊ ክዋንግ ሁንም በአዲሱ ዙር ከተጠቁት መካከል 107ቱ ከሳቸው ጋር የተያያዘ መሆኑም ተገልጿል።

    የደቡብ ኮሪያን መንግሥት በመተቸት የሚታወቁት አወዛጋቢው ፓስተር መመሪያውን ተላልፈውም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ምዕመናን የተሳተፉበት ሰልፍ አካሂደዋል። በመዲናዋ ሴዑል በተደረገው በዚህ ፀረ-መንግሥት ተቃውሞም ላይም አስር ሺህ ሰዎች ተሳትፈዋል።

    የአገሪቱ ጤና ኃላፊዎች ከህሙማኑ ጋር ንክኪ ያላቸውን የምዕመናኑን ዝርዝር አልሰጥም በማለት እምቢተኛነተኛውን አሳይተዋል በማለት ፓስተሩን ወንጅለዋቸዋል።

    ፕሬዚዳንት ሙን ጄ ፓስተሩን በከፍተኛ ሁኔታ የተቿቸው ሲሆን ለዚህም ኃላፊነት ለጎደላቸው ተግባር መንግሥት የሚያደርገው ነገር እንዳለ ጠቆም አድርገዋል።

    “ህዝባችንን አደጋ ውስጥ ያስገባ ይቅር የማይባል ተግባር” ነው በማለት ፌስቡክ ገፃቸው ላይ መልዕክት ያሰፈሩ ሲሆን በተሳታፊዎችም ላይ መንግሥታቸው እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቀዋል።

  4. የኒው ዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የቀጣዩ ወር ምርጫ ይራዘም እያሉ ነው

    የኒው ዚላንድ ምክትል ጠ/ሚ

    የኒው ዚላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በቀጣዩ ወር ሊካሄድ እቅድ የተያዘለት ምርጫ የኮሮናቫይረ ስወረርሽኝ እንደ አዲስ በማገርሸቱ ምክንያት ይራዘም ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

    ምክትሉ ዊንስተን ፒተርስ ወረርሽኙ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ እንዳይካሄድ እንቅፋት ሊሆን ይችላል ይላሉ።

    ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ማለታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደን ተጨማሪ ጫና ነው እየተባለ ነው።

    ጠቅላይ ሚኒስትሯ ሰኞ ጠዋት ቀጣዩን ምርጫ አስመልክተው መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

    መቶ ቀናት ያክል ምንም ዓይነት ኮሮናቫይረስ ያለው ሰው ያልተገኘባት ኒው ዚላንድ ወረርሽኙ እንደ አዲስ ማገርሸቱን ተከትሎ የእንቅስቃሴ ገደብ ጥላለች።

    ዕሁድ ይፋ በተደረገው መረጃ መሠረት 13 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንዳለባቸው ተረጋግጧል። ይህም ጠቅላላ ቁጥሩን 69 አድርሶታል።

  5. በ24 ሰዓታት በዓለም ከፍተኛ የተበለ የኮሮናቫይረስ ሕሙማን ቁጥር ተመዘገበ

    ኮሮናቫይረስ

    የአለም ጤና ድርጅት እንዳሳወቀው ባለፉት ሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ ከፍተኛ የተባለው 294 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

    ይህንንም ተከትሎ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ከ21 ሚሊዮን በላይ አድርሶታል ሲል ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ያጣው ዘገባ ጠቁሟል።

    771 ሺህ የአለማችን ዜጎችም በኮሮናቫይረስ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል።

    በቫይረሱ በተያዙም ሆነ በሟቾች ቁጥር ቀዳሚ በሆነችው አሜሪካ 5 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ የ170 ሺህ ሰዎችም ህይወት ተቀጥፏል።

  6. በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 1652 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ

    በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በ22 ሺህ 252 ናሙና ላይ በተደረገ ምርመራ 1652 ሰዎች ላይ ኮቪድ-19 መገኘቱ ተረጋገጠ። ይህም እስካሁን ከተመዘገበው ከፍተኛው ቁጥር ነው።

    የጤና ሚንስትር እና የሕብረተሰብ ጤና ተቋም በጋራ ባወጡት መግለጫ መሠረት እስካሁን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 28 ሺህ 894 ደርሰዋል።

    በአንድ ቀን 17 ሰዎች በወረርሽኙ ሳቢያ ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ የሟቾች ቁጥር 509 ደርሷል።

    ባለፉት 24 ሰዓታት 377 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸው ተገልጿል። ይህም አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 12 ሺህ 073 አድርሶታል።

    ኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን 589 ሺህ 694 ናሙና ላይ ምርመራ ተካሂዷል።

    አሃዝ
  7. በሺዎች የሚቆጠሩ ተጓዦች ለይቶ ማቆያ ላለመግባት እየተጣደፉ ነው

    አየር መንገድ

    ከቅዳሜ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነውን የዓለም አቀፍ ተጓዦች አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ሕግ ለማምለጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ዩናይትድ ኪንግደም እየተጣደፉ እየሄዱ እንደሆነ ተዘግቧል።

    ከኔዘርላንድስ፣ ሞናኮ፣ ማልታ፣ ተርክስ ኤንድ ካይኮስ እንዲሁም አሩባ የሚሄዱ ተጓዦችም ለ14 ቀናት ራሳቸውን ለይተው የመቆየት ግዴታ አለባቸው።

    ዩሮተንል የተባለው የባቡር ድርጅት ባለፈው አርብ ትኬቶች ተሽጠው እንዳለቁ አስታውቋል። የአየር ጉዞም ቢሆን ደንበኞች መብዛታቸውን ተከትሎ የዋጋ ጭማሪ ታይቶበታል።

    ፈረንሳይ ግን ይህ ውሳኔ ሌላ መዘዝ ሊኖረው ይችላል ስትል አስጠንቅቃለች። ኔዘርላንድስም ብትሆን በጣም አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ወደ ዩኬ መሄድ የቫይረሱን ስርጭት ሊያባብስ ይችላል ብላለች።

    የሕጉ ቀነ ገደብ ከመድረሱ በፊት ደግሞ በርካቶች በተጋነነ ዋጋ ጭምር የባቡር፣ የአውሮፕላን እና የመርከብ ትኬቶችን ገዝተው ለመጓዝ እየተጣደፉ ነው።

  8. በዓሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ኮርያውያን የተቃውሞ ሰልፍ ወጥተዋል

    ተቃውሞ

    የጤና ዘርፉ ኃላፊዎች በርካታ ሰዎች በአንድ ቦታ እንዳይሰበሰቡ ቢያሳስቡም በዓሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ኮርያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል።

    በደቡብ ኮርያ በ24 ሰዓታት 166 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተገልጿል። ይህም ባለፉት አምስት ወራት ከተመዘገበው ከፍተኛው ነው።

    የሴዑል ባለሥልጣኖች ብዙ የተቃውሞ ሰልፎች እንዳይካሄዱ በፍርድ ቤት ማሳገድ ችለዋል። የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት የወጣውን ሕግ ይተላለፋሉ በሚል አንዳንድ ሰልፎችን ቢያሳግዱም፤ እንዲካሄዱ የተፈቀዱ የተቃውሞ ሰልፎችም ነበሩ።

    የመንግሥትን ፓሊሲ በመቃወም ሰልፍ ካስተባበሩ አንዱ የሆነው ቤተ ክርስቲያን 130 አባላት ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።

    የቤተ ክርስቲያኑ ፓስተር ለደጋፊዎቻቸው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ፤ ፖሊስ ከጠበቀው በላይ ሰልፈኞች ተገኝተዋል።

  9. ሕንድ ክትባት በጅምላ ለማምረት ዝግጁ ነኝ አለች

    ሞዲ

    የሕንድ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ፤ ሳይንቲስቶች ክትባት ይመረት ካሉ አገሪቱ ክትባት በጅምላ ለማምረት ዝግጁ መሆኗን ተናገሩ።

    የሕንድን የነፃነት ቀንን አስመልክተው ባደረጉት ንግግር “ሦስት ክትባቶች ላይ ምርምር እየተደረገ ነው” ብለዋል።

    “በጅምላ ከማምረት ባሻገር ክትባቱን ለመላው ሕንድዳውያን የምናደርስበትን መንገድ ወጥነናል” ሲሉም አክለዋል።

    ሕንድ በቫይረሱ ሳቢያ በሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዓለም አራተኛ ናት። እስካሁን ከ49 ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ ያሳያል።

  10. በቫይረሱ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ከ765 ሺህ አልፈዋል

    መጓጓዝ

    በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ መሠረት በመላው ዓለም በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ21 ሚሊዮን 176 ሺህ አልፏል። በወረርሽኙ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ደግሞ ከ765 ሺህ አልፈዋል።

    ከተለያዩ አገሮች የተውጣጡ ዘገባዎችን እንቃኝ፦

    ዩናይትድ ኪንግደም፡ ከኔዘርላንድስ፣ ሞናኮ፣ ማልታ፣ ተርክስ ኤንድ ካይኮስ እንዲሁም አሩባ የሚሄዱ ተጓዦች ለ14 ቀን ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተወስኗል።

    ደቡብ አፍሪካ፡ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ከተጣለ በኋላ በነበሩት ሦስት ወራት ወንጀል 40 በመቶ መቀነሱ ተዘግቧል።

    ኒው ዚላንድ፡ በበሽታው የተያዙ ሰባት ሰዎች ተመዝግበዋል። ኦክላንድ ከተማ ላይ የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብም ለሁለት ሳምንት ተራዝሟል።

    አውስትራሊያ፡ በቪክቶሪያ ከተማ 303 በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል። አራት ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ ወረርሽኙ ከፍተኛ ነጥቡን በማለፉ ማኅበረሰቡ እንዲጠነቀቅ ማሳሳቢያ ተሰጥቷል።

  11. ሩሲያ የኮቪድ-19 ክትባት ማምረት ጀመረች

    ክትባት

    የሩሲያ ጤና ሚኒስትር መሥሪያ ቤት ለኮሮናቫይረስ የተዘጋጀውን ክትባት ማምረት መጀመራቸውን አስታወቀ።

    ሚኒስቴሩ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በብዛት የሚመረተው ክትባት በያዝነው ወር መጨረሻ ላይ መከፋፈል እንደሚጀምር ገልጿል።

    ቢሆንም ግን በርካታ የዘርፉ ተመራማሪዎች ሩሲያ በችኮላ ያመረተችው ክትባት ሌላ መዘዝ ይዞ እንዳይመጣ ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።

  12. ኮሮናቫይረስ ኢትዮጵያ

    አህጉረ አፍሪካ የመጀመሪያው ሰው በኮሮናቫይረስ ተይዞብኛል ብላ ካወጀች እነሆ ግማሽ ዓመት ሆነ።አህጉሪቱ ውስጥ የመጀመሪያ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ይፋ የተደረገው ግብፅ ውስጥ ነው። ይህ ዜና ከተሰማ በኋላም ቢሆን ወረርሽኙ አፍሪካ ላይ ብርቱ ክርኑን ወዲያው አላሰረፈም ነበር። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአህጉሪቱ ሃገራት በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው።

    ተጨማሪ ያንብቡ
    next
  13. በኮሮናቫይረስ ምክንያት በደቡብ አፍሪካ ወንጀል 40 በመቶ ቀነሰ

    የተዘጋ የመጠጥ መደብርና ፖሊስ

    በደቡብ አፍሪካ የኮሮረናቫይረስን ተከትሎ በተጣለው እንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ በአገሪቱ ይፈጸም የነበረው የወንጀል መጠን 40 በመቶ መቀነሱን መንግሥት ያወጣው መረጃ አመለከተ።

    የፖሊስ ሚኒስትሩ ከባለፈው ሚያዝያ እስከ ሰኔ ባለው ጊዜ ውስጥ ጾታዊ ጥቃትና በጦር መሳሪያ የታገዘ ዝርፊያን ጨምሮ ሌሎች ወንጀሎች በእጅጉ ቀንሰዋል ብለዋል።

    ሚኒስትሩ አክለውም አወዛጋቢነቱ ቢቀጥልም ከወረርሽኙ መስፋፋት ጋር ተያይዞ በአልኮል ሽያጭ ላይ የተደረገው ክልከላ ለወንጀሎች መቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል ካሉ በኋላ፤ በአልኮል መሸጫዎች ላይ የሚፈጸም ዝርፊያና ጥቃት ግን ጨምሯል ብለዋል።

    ደቡብ አፍሪካ በዓለማችን ከፍተኛ ወንጀል ከሚፈጸምባቸው አገራት ተርታ ትመደባለች። በተጨማሪም በአፍሪካ በኮሮረናቫይረስ ከተያዙ ሰዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የሚገኙት በደቡብ አፍሪካ ነው።

    በአገሪቱ ከ500 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 11 ሺህ ሰዎች ደግሞ በዚሁ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። ነገር ግን ቁጥሩ እንዲህ ከፍ ሊል የቻለው በተገቢው መንገድ በርካቶችን መመርመር በመቻሏ እንደሆነ ተገልጿል።

  14. ኮቪድ-19 በአንጎላችን ላይ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት ምንድን ነው?

    የአንጎል የስካነር ምስል

    አዲሱ ኮሮናቫይረስን የተመለከቱ ብዙ ያልታወቁ ነገሮች እንዳሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። የበሽታውን ምንነት፣ ስለመተላለፊያ መንገዶቹና ስለሚያስከትለው ጉዳት ምርምሮች እየተደረጉ ነው።

    ኮቪድ-19 የመተንፈሻ አካላት ላይ ብቻ ጉዳትን የሚያስከትል ወረርሽኝ ላይሆን ይችላል እየተባለ ነው። ምልክቶቹም እንዲሁ ሊለያዩ ይችላሉ።

    እያንዳንዱ ሳምንት ባለፈ ቁጥር ኮሮናቫይረስ ዘርፈ ብዙ አእምሯዊና አካላዊ ጉዳቶችን ማስከተል ይጀምራል።

    ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የተረጋገጡ በርካታ ሰዎች በመጀመሪያ አካባቢ ብዙም የሚያሰጋ ህመም የማይሰማቸው ሲሆን፤ ቀስ በቀስ ግን ማስታወስ አለመቻልና ድካምን የመሳሰሉ ጠንከር ያሉ ምልክቶች ማሳየት ይጀምራሉ።

    ፖል ማይልሪያ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሁለት ከባድ የሚባሉ ስትሮኮች [የአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ] አጋጥመውታል። ብዙ ያልተነገረለት ኮቪድ-19 በአንጎላችን ላይ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት ምንድን ነው?

  15. ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኮሮናቫይረስ ምርመራ አደረገች

    ምርመራ

    በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ወራት ከተካሄዱት ሁሉ ከፍተኛው የኮሮናቫይረስ ምርመራ በአንድ ቀን ውስጥ ተካሄደ።

    ነሐሴ 08 ቀን 2012 ዓ. ም. በወጣው የወረርሽኙ መግለጫ ላይ እንደተመለከተው በ24 ሰዓታት ውስጥ ለ17 ሺህ 323 ናሙናዎች ምርመራ ተደርጓል። ከእነዚህም መካከል 1038 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱ ተገልጿል።

    እስካሁን ድረስ በአገሪቱ በአጠቃላይ በ567 ሺህ 442 ናሙናዎች ላይ የወረርሽኙ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከእነዚህ መካከልም 27 ሺህ 242 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል።

    በበሸታው መያዛቸው ከታወቁት ሰዎች ውስጥ እስካሁን ድረስ 11 ሺህ 660ው ማገገማቸው በመገለጹ በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች የተጣራ ቁጥር 15 ሺህ 088 ነው።

    ከበሽታው ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች አሃዝም ከዕለት ዕለት እየጨመረ ሲሆን ባለፉት አምስት ወራት ለሞት የተዳረጉት ሰዎች ቁጥር 492 ደርሷል።

    ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ ምርመራ በማድረግ ከሚጠቀሱ አገራት ውስጥ የምትገኝ ሲሆን በዙሪያዋ ካሉ አገራት መካከል ከኬንያ በመቀጠል በርካታ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ለመለየት ችላለች።

  16. የዕለተ ቅዳሜ ነሐሴ 09/2012 ዓ.ም የቢቢሲ አማርኛ የቀጥታ ዘገባ ገጽ

    ቢቢሲ አማርኛ

    ጤና ይስጥልኝ!

    ይህ ከኢትዮጵያና ከዓለም ዙሪያ ስለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተለያዩ ዘገባዎች በትኩሱ የሚቀርቡበት የቢቢሲ አማርኛ የቀጥታ ዘገባ ገጽ ነው።

    ከዕለት ዕለት በኢትዮጵያ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ስላለውና የወቅቱ የዓለማችን አሳሳቢ የጤና ችግር ስለሆነው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከአገር ውስጥና ከዓለም ዙሪያ የሚሰባሰቡ ትኩስ ዜናና መረጃዎችን በቀጥታ የዘገባ ገጻችን ላይ እናቀርባለን።

    እናንተም ባገኛችሁት አጋጣሚ ሁሉ ይህንን የቀጥታ ዘገባ ገጻችንን እንድትጎበኙ በአክብሮት እንጋብዛለን።

  17. የኮሮናቫይረስ ማሻቀቡን ተከትሎ የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር ወጣቱን እየተማፀኑ ነው

    ግሪክ

    የኮሮናቫይረስ የማህበረሰብ ስርጭት እየጨመረባት ባለችው ግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ወጣት ዜጎቻቸው እንዲጠነቀቁ ተማፅነዋል።

    "የቫይረሱ ስርጭት ወጣት ከሆኑ ዜጎቻችን ጋር ቁርኝት እንዳለው ተረድተናል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከውጭ አገራት የሚመጡ መንገደኞች ጭምብል እንዲያጠልቁና ተጋላጭ ከሚባሉ ማህበረሰቦችም ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳይኖራቸው ጠይቀዋል።

    "ወጣቶቹን ልማፀን እፈልጋለሁ። እኔም በናንተ እድሜ የሆኑ ልጆች አሉኝ። እባካችሁ ተጠንቀቁ። በሽታው የማይዛችሁ አይምሰላችሁ። ለወላጆቻችሁና አያቶቻችሁ አስቡ" ብለዋል።

    በአገሪቷም አዳዲስ መመሪያዎች የወጡ ሲሆን ሬስቶራንቶችና መጠጥ ቤቶች ከሌሊት ጀምሮ በአቴንስ፣ ተሰሎንቄ፤ ምይኮኖስ፣ ሳንቶሪኒ፣ ኮርፉ በመሳሰሉ ደሴቶች እንዲዘጉ ተወስኗል።

  18. ኢትዮጵያ፡ ተጨማሪ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ተያዙ

    የኮሮና መግለጫ

    በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ17 ሺህ 323 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ 1038 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ሲል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መግለጫ አትቷል።

    በአሁኑ ወቅት በፅኑ የታመሙ ሰዎች ቁጥር 195 ቢሆንም ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር ከ15 ሺህ በላይ ነው።

    ከዚህ በተጨማሪ 13 ተጨማሪ ሰዎች ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ሕይወታቸው አልፏል። ይህም ጠቅላላ የሟቾች ቁጥርን 492 አድርሶታል።

    ጠቅላላ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 11 ሺህ 660 ሲሆን ይህም ባለፉት 24 ሰዓታት ያገገሙ 232 ሰዎችን ጨምሮ ነው።

    ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማካሄድ ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ ከ567 ሺህ በላይ ናሙናዎች ተመርምረዋል። 27 ሺህ 242 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸውም ተረጋግጧል።

    ያለፉት 24 ሰዓታት ምርመራ ኢትዮጵያ እስከዛሬ ካደረጋቻቸው ከፍተኛው ነው።

  19. ኪም ጁንግ ኡን በኮሮናቫይረስ ፍራቻ እርዳታ አልቀበልም አሉ

    የሰሜን ኮሪያው ጠቅላይ ገዥ ኪም ጆንግ ኡን

    በጎርፍ አደጋ የተጠቃችው ሰሜን ኮሪያ ከአለም አቀፉ የሚቀርብ ማንኛውንም እርዳታ በኮሮናቫይረስ ፍራቻ እንደማትቀበል መሪዋ ኪም ጆንግ ኡን አስታውቀዋል።

    እርዳታን መቀበል ህዝቡን ለኮሮናቫይረስ ሊያጋልጠው ስለሚችልም እርዳታ እንዲታገድ ትዕዛዝ አስቀምጠዋል።

    የአገሪቱ ሚዲያ እንደዘገበው ኪም ጆንግ ኡን ከፍተኛ ኃላፊዎቻቸውን ሰብስበው የአገሪቷ ድንበሮች እንዲዘጋ በተጨማሪ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

    ሰሜን ኮሪያ እስካሁን ድረስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው በአገሪቷ አላገኘሁም ብትልም የጤና ባለሙያዎች ማመን ያዳግታል በማለት ጥርጣሬያቸውን አስቀምጠዋል።

    ኬሶንግ በተባለችው ከተማ በኮሮናቫይረስ የተጠረጠረ ሰው መገኘቱን ተከትሎ ከተማዋ ከማንኛውም እንቅስቃሴ እንድትታገድ ቢደረግም ገደቡ በዛሬው ዕለት ተነስቷል።

    ሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ በተባለ የሞንሱን ዝናብ የተመታች ሲሆን ከሃያ ሰዎች በላይ ሞተዋል፤ 16 ሺህ ቤቶችም ወድመዋል።

  20. የማዳጋስካሩ ፕሬዚዳንት አንድሪ ራጆይሊና

    በሕንድ ውቅያኖስ ላይ የምትገኘው ደሴቲቷ አገር ማደጋስካር ባለፈው ወር ብቻ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአራት እጥፍ የጨመረ ሲሆን፣ እስካሁን 13 ሺ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። 162 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን እንዳጡ የአገሪቱ መንግስት አስታውቋል።

    ተጨማሪ ያንብቡ
    next