BBC News, አማርኛ - ዜና
BBC News Amharic Top Stories
የብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ አባላት በሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት እና አሳሳች የፌስቡክ ዘመቻዎች ላይ መሳተፋቸውን የቢቢሲ ምርመራ አረጋገጠ
በገዢው ብልፅግና ፓርቲ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስር የሚንቀሳቀሱ እና ‘የሚዲያ ሠራዊት’ የሚል መጠሪያ ያላቸው የፓርቲው አባላት፤ መንግሥትን በሚተቹ እና በሚቃወሙ ግለሰቦች ላይ በፌስቡክ በተደረጉ የሐሰተኛ መረጃ እና በተቀናጁ ዘመቻዎች ላይ እንደተሳተፉ ቢቢሲ ያደረገው ምርመራ አረጋገጠ።
እስራኤል በኢራን ላይ የአጸፋ ጥቃት ፈጸመች
እስራኤል ባለፈው ቅዳሜ ኢራን ለፈጸመችባት የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃት ዛሬ ማለዳ ላይ የአጸፋ ጥቃት መፈጸሟን የኢራን መገናኛ ብዙኃን እና የአሜሪካ ባለሥልጣናት አስታወቁ።
በቦኮሃራም የታገተችው ናይጄሪያዊት ተማሪ ከ10 ዓመት በኋላ ሦስት ልጆችን ወልዳ ነጻ ወጣች
ከአስር ዓመት በፊት በቦኮሃራም ታጣቂዎች ታግተው ከነበሩ ሴቶች መካከል አንዷ የሦስት ልጆች እናት ሆና በናይጄሪያ መንግሥት ወታደሮች ነጻ ወጣች።
ኢትዮጵያ፡ 56 በመቶ የሚሆኑ የሁለተኛ እና ሦስተኛ ክፍል ተማሪዎች ፊደል መለየት እንደማይችሉ ጥናት አመለከተ
በኢትዮጵያ ከሚገኙ የሁለተኛ እና ሶስተኛ ክፍል ተማሪች 56 በመቶዎቹ ምንም ዓይነት ቃል ማንበብ እንደማይችሉ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባደረገው ጥናት አመልክቷል። አገልግሎቱ በጥናቱ ተሳተፊ ካደረጋቸው የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ቢያንስ አንድ ቃል ማንበብ የሚችሉ 37 በመቶ የሚሆኑት ብቻ እንደሆኑ በአገልግሎቱ የትምህርት ምዘናና ምርምር መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤፋ ጉርሙ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ገልጸዋል። የተቀሩት 63 በመቶዎቹ አንድም ቃል ማንብብ የማይችሉ (Zero renderers) ናቸው።
በኬንያ በደረሰ የሄሊኮፕተር አደጋ የአገሪቱ ኢታማዦር ሹም እና ሌሎች መኮንኖች ሞቱ
የኬንያ ጦር አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ኦሞንዲ ኦጎላ በምዕራብ የአገሪቱ ክፍል ይበሩበት የነበረው ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ ሕይወታቸው ማለፉን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አስታወቁ።
የዩክሬን ፕሬዝዳንትን ለመግደል ከሩሲያ ጋር ሲያሴር ነበር የተባለ ግለሰብ ፖላንድ ውስጥ ተያዘ
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቭሎድሚር ዜሌንስኪን ለመግደል ከሩሲያ የደኅንነት አገልግሎት ጋር አሲሯል የተባለ ግለሰብ ፖላንድ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለ።
በጎርፍ በተጥለቀለቀችው ኤምሬትስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?
ከሁለት ቀናት በፊት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና በሌሎች አገራት አውሎ ንፋስ የቀላቀለው ከባድ ዝናብ የጎርፍ መጥለቅለቅ አስከትሏል። በዩናይትድ አረብ ኤምሬት ታሪክ በ75 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ መሆኑ የተመዘገበለት ከባድ ዝናብ ተሽከርካሪዎችን ጠርጎ ከመውሰድ በተጨማሪ የተለያዩ ንብረቶች ላይ ጉዳቶች አድርሷል። ለመሆኑ በነዚህ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?
ኢራን እና እስራኤል ለምን ደመኛ ጠላቶች ሆኑ?
ኢራን ከግብፅ ቀጥላ ለእስራኤል እውቅና በመስጠት ሁለተኛዋ እስላመዊ አገር ነበረች። ነገር ግን ከኢራን እስላማዊ አብዮት በኋላ ይህ ግንኙነት ተበላሽቶ ከአምስት አስርታት በላይ በጠላትነት እየተያዩ ቆይተዋል። ለመሆኑ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ወደ ደመኛ ጠላትነት ለምን ተሸጋገረ?
ጀርመን የሩሲያ ሰላይ ናቸው ያለቻቸውን ሁለት ሰዎች መያዟን አስታወቀች
ጀርመን ለዩክሬን የምትሰጠውን ወታደራዊ ድጋፍ ለማደናቀፍ ሲያሴሩ ነበር የተባሉ በስለላ የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች ደቡባዊ ግዛቷ ባቫሪያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በሲድኒ በስለት የተወጉት የኦርቶዶክስ ጳጳስ ጥቃት አድራሹን “ይቅር ብያለሁ” አሉ
ባለፈው ሰኞ በአውስትራሊያ ሲድኒ ከተማ በቀጥታ በሚተላለፍ ሰብከት ላይ ሳሉ በስለት ጥቃት የደረሰባቸው አቡነ ማር ማሪ ኢማኑኤል በፍጥነት እያገገሙ እንደሆነ ገልጸው፣ ጥቃቱን እንዳደረሰ ለተጠረጠረው ግለሰብም ይቅርታ እንዳደረጉ ተናግረዋል።
ቪዲዮ, አንድ ዓመት በሞላው ጦርነት ለውስብስብ ችግር የተጋለጡት ሱዳናውያን ክርስቲያኖችርዝመት, 1,54
ባለፈው ዓመት የተቀሰቀሰው የሱዳን ጦርነት ክርስቲያኖችን አጣብቂኝ ውስጥ ከቷቸዋል። በጦርነቱ መጀመሪያ አካባቢ ክርስቲያኖች በተለየ መልኩ ተጠቅተዋል የሚሉ መረጃዎች ሲወጡ ነበር። አብያተ ክርስቲያናት ተዘርፈዋል፤ አንዳንዶቹም በከባድ መሣሪያ ጥቃት ደርሶባቸዋል። ከአንድ ዓመት በኋላ ብዙዎቹ ወደ ግብፅ ሲሰደዱ፣ ቀሪዎቹም ተጠልለው ከሚገኙበት ፖርት ሱዳን ለመሰደድ አማራጮችን እየፈለጉ ነው።
ስዊድን ፆታን በሕጋዊ መንገድ የመቀየሪያን እድሜን ከ18 ወደ 16 ዝቅ አደረገች
የስዊድን ፓርላማ ፆታን በሕጋዊ መንገድ የመቀየሪያን እድሜ ከ18 ወደ 16 ዝቅ በማድረግ ሂደቱን የሚያቀል ህግ አጸደቀ።
አነጋጋሪ ጉዳይ
“ህወሓት የፕሪቶሪያውን ስምምነት ጥሶ አራተኛ ዙር ወረራ ፈጸመ” ሲል የአማራ ክልል ከሰሰ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ህወሓት የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመጣስ አራተኛ ዙር ወረራ በሕዝብ በላይ ፈጽሟል ሲል ከሰሰ። የክልሉ መንግሥት ዛሬ የሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫው “ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ መማር የተሳነው ህወሓት የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመጣስ ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል” ብሏል።
ለኢትዮጵያ ከተጠየቀው 3.24 ቢሊዮን የገንዘብ ድጋፍ 610 ሚሊዮን ቃል ተገባ
በኢትዮጵያ ላለው የከፋ የሰብዓዊ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት በኢትዮጵያ መንግሥት እና ዓለም አቀፍ አጋሮች በተጠረ የገንዘብ ማሰባሰብ ሥነ ሥርዓት 610 ሚሊዮን ዶላር ተሰበሰበ።
ወደ የኦሮሚያ አካባቢ አንመለስም ያሉ ተፈናቃዮች የምግብ እርዳታ “ተከለከልን” አሉ
የደኅንነት ስጋት አድሮባቸው ዳግም ወደ ደብረ ብርሃን የተመለሱ እና ቀድሞውኑም ለመመለስ ፈቃደኛ ያልሆኑ በሺህ የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች የምግብ እርዳታ እንዳይሰጣቸው መከልከሉን ተፈናቃዮች እና አስተባባሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።
አላማጣ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት እና በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆኗን የከተማዋ ከንቲባ ተናገሩ
ካለፈው ሳምንት ቅዳሜ ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድባቸው በነበሩ የራያ አላማጣ አካባቢዎች አቅራቢያ የምትገኘው አላማጣ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት እና በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆኗን የከተማዋ ከንቲባ አቶ ኃይሉ አበራ ለቢቢሲ ተናገሩ።
በአዲስ አበባ የተገደሉ ‘የፋኖ አባላት’ አስከሬን ይሰጠን ጥያቄ እስካሁን ምላሽ አለማግኘቱን ወላጆቻቸው ተናገሩ
በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ከቀናት በፊት መገደላቸው የተነገረው የፋኖ አባላት ወላጆች የልጆቻቸው አስከሬን እንዲሰጣቸው ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱን ለቢቢሲ ተናገሩ። ባለፈው ሳምንት አርብ ሚያዝያ 4/2016 ዓ.ም. የተገደሉት ናሁሰናይ አንዳርጌ እና አቤኔዘር ጋሻው ከሞቱ አራተኛ ቀናቸውን ቢያስቆጥሩም አስከሬናቸውን እስካሁን ማግኘት እንዳልቻሉ እናቶቻቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል።
አወዛጋቢ የሚባሉት የአሲሪያን ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን አቡን ማር ማሪ ኢማኑዔል ማን ናቸው?
አቡነ ማር ማሪ ያደጉት በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ ሲሆን፣ በልጅነታቸው ነው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ አውስትራሊያ ያቀኑት። ክራይስት ዘ ጉድ ሼፐርድ ቤተ-ክርስቲያን ድረ-ገፅ እንደሚጠቁመው አባ ማር ማሪ ኢማኑዔል በአውሮፓውያኑ 2009 ቄስ፤ ቀጥሎ ደግሞ በ2011 አቡን ሆነው ተቀብተዋል።
ኢራን በእስራኤል ላይ በፈጸመችው ጥቃት ማን አተረፈ? ማንስ ከሰረ?
ባለፈው ቅዳሜ ሌሊት ኢራን በእስራኤል ላይ በሚሳኤል እና በድሮኖች የፈጸመችው ጥቃት በመላው ዓለም ስጋት ፈጥሯል። ሁለቱም አገራት ከዚህ ፍጥጫ የሚፈልጉትን ዓላማ ለማሳካት ጥረት እያደረጉ ሲሆን፣ ለመሆኑ ከቅዳሜው ጥቃት ኢራን ወይስ እስራኤል አትራፊ ሆኑ?
አደገኛ በመሆኑ ከገበያ እንዲሰበሰብ ስለተባለው የህጻናት የሳል ሽሮፕ ምን እናውቃለን?
ቢያንስ አምስት የሚሆኑ የአፍሪካ አገራት የተወሰኑ የጆንሰን ኤንድ ጀንሰን የሳል ሽሮፖች ከገበያ እንዲሰበሰቡ አዘዋል። “እጅግ ከፍተኛ” መርዛማ እና የመግደል አቅም ያለው ዳይትሊን ግላይኮል የተባለውን ንጥረ ነገር በምርመራ እንዳገኙበት ገልጸዋል።
ጆ ባይደን ከዶናልድ ትራምፕ፡ ለፕሬዝዳንትነት አሸናፊውን የሚለዩ አራት ወሳኝ ነጥቦች
ትራምፕ ዘመቻቸውን ወደ ኋላ ሊጎትትባቸው የሚችለው ጉዳይ እየቀረበባቸው ያለው ክስ ነው። አልፎም የሚያሰሟቸው አወዛጋቢ ንግግሮች እና ያለፈውን ምርጫ ውጤት ለመቀበል ማመንታታቸው እንደ ድክመት ይነሳባቸዋል። ባይደንም ቢሆኑ ከድክመት ነፃ አይደሉም።
ከ50 በላይ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ስደተኞች በሱዳን ኃይሎች እንደምርኮኛ መያዛቸው ተነገረ
በሱዳን በኩል ወደ ሊቢያ ለማቋረጥ ሲሞክሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ወጣት ስደተኞች ለአንድ ዓመት በቆየው የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ በሚገኙ ተዋጊ ኃይሎች እንደ ምርኮኛ ተይዘው እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ።
ኢራን፣ እስራኤል ላይ ጥቃት ከሰነዘረች በኋላ የዓለም ነዳጅ እና ወርቅ ዋጋ ቀነሰ
ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ኢራን እስራኤል ላይ የጥቃት እርምጃ ከወሰደች በኋላ ከትናንት ሰኞ ጀምሮ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ቅናሽ ታይቷል።
ወደ ባንኮች ያዘዋወሩትን ገንዘብ መመለስ ባለመቻላቸው አጣብቂኝ ውስጥ የገቡት ተማሪዎች
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በገንዘብ ዝውውር ሥርዓቱ ላይ አጋጥሞት በነበረው ችግር ምክንያት በርካታ ደንበኞቹ የራሳቸው ያልሆነ የገንዘብ መውሰዳችን አሳውቆ አብዛኛውን ገንዘብ ማስመለሱንም መግለጹ ይታወሳል። ያልመለሱትን ደግሞ ፎቷቸውን ጨምሮ መረጃቸውን በተለያየ መንገድ ይፋ አድርጓል። በዚህ ጉዳይ ውስጥ ስማቸው በስፋት ሲነሳ የነበሩ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መውደቃቸውን እየተናገሩ ነው።
ከየፈርጁ
በእስራኤል ጥቃት በአንድ ላይ ስለተገደሉት የሐማስ መሪ ልጆች እና የልጅ ልጆች ምን እናውቃለን?
የሐማስ የፖለቲካ መሪ እስማኤል ሃኒዬህ ሦስት ልጆች እና አራት የልጅ ልጆቻቸው ረቡዕ ዕለት እስራኤል ጋዛ ውስጥ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ተገድለዋል። ለመሆኑ የተገደሉት የሃንዬህ ልጆች በሐማስ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፎ አላቸው?
ቡና እንዴት በዓለማችን በብዙዎች የሚወደድ አነቃቂ ፍሬ ሊሆን ቻለ?
እንቅልፍ ከማትተኛው የኒው ዮርክ ከተማ እስከ ኢትዮጵያ ተራሮች ድረስ ዝናው የናኘ ነው፤ ቡና። ሚሊዮኖች ሳይጎነጩት መዋል አይቻላቸውም። ቡና ለ15 ክፍለ ዘመናት የሰው ልጆች ባህል ማዕከል ሆኖ ኖሯል። አንዳንዶች የ17ኛው እና የ18ኛው ክፍለ ዘመን አብርሆት ከቡና ነው የመነጨው ይላሉ።
እስራኤል የምትመካበት የሚሳኤል እና የሮኬቶች ማምከኛ ‘አይረን ዶም’ ምንድን ነው?
እስራኤል ከየትኛውም ወገን የሚሰነዘሩባትን የሚሳኤል እና የሮኬት ጥቃቶችን ለመከላከል “አይረን ዶም” የተባለውን የአየር ላይ ጥቃት ማምከኛ ሥርዓትን ትጠቀማለች።
ዩኬ የህጻናት ደፋሪዎች ወላጅነት መብትን ይነጥቃል የተባለ ህግ ልታወጣ ነው
ዩናይትድ ኪንግደም በከባድ ወሲባዊ ጥቃቶች የተከሰሱ ህጻናት ደፋሪዎች በልጆቻቸው ላይ ያላቸውን መብትይነፍጋል የተባለ አዲስ ህግ ልታወጣ ነው።
ኢትዮጵያ ፆታዊ ጥቃት ፈጻሚዎችን ከሥራ እና ከማኅበራዊ ግልጋሎቶች የሚያገል ምዝገባ ልትጀምር ነው
የኢትዮጵያ መንግሥት ፆታዊ ጥቃት ፈጻሚዎችን የሚመዘግብ ሥርዓት ሊጀምር መሆኑን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። ምዝገባው ፆታን መሠረት አድርገው የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከል እና ለመቀነስ ያለመ ነው የተባለ ሲሆን፣ በተለይ “ወሲባዊ ጥቃቶች ላይ ትኩረት” እንደሚያደርግ ተነግሯል።
የተረሳው ግጭት እና ከአስከፊ የረሃብ ቀውስ አፋፍ ላይ የምትገኘው ሱዳን
በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (አርኤስኤፍ) መካከል ግጭት ተቀስቅሶ አገሪቱን ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ከዘፈቋት አንድ ዓመት ሞላ። በዋና ከተማይቱ ካርቱም የተጀመረው ሁከት እና ብጥብጥ በመላ አገሪቱ ተዛምቷል። ጦርነቱ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት ምክንያት ሲሆን ህንፃዎች እና መሠረተ ልማቶችም ወድመዋል።
አንድ ሠራተኛ በመቀለ አይደር ሆስፒታል ውስጥ በሚሊዮኖች የሚገመት ዋጋ ባላቸው የህክምና መሳሪያዎች ላይ ጉዳት አደረሰ
በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ የሚገኘው የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ባልደረባ በሚሊዮኖች የሚገመት ዋጋ ያላቸው በርካታ የህክምና መሳርያዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የሆስፒታሉ ዳይሬክተር ዶ/ር አብርሃ ገብረግዚአብሄር ለቢቢሲ ተናገሩ።
ቪዲዮ, ቢቢሲ ያጋለጠው የአፍሪካውያን የቤት ሠራተኞች ሰቆቃ በባሕረ ሰላጤዋ አገርርዝመት, 5,25
በባሕረ ሰላጤው አገራት ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ የቤት ውስጥ ሠራተኞች ይገኛሉ። ኑሮን ለማቃናት ወደ አረብ አገራቱ ያቀኑት አፍሪካውያን ግን ሥራ እና ኑሮ ቀላል አልሆነላቸውም። አብዛኞቹ በአሠሪዎቻቸው ጉልበታቸው የሚበዘበዝ፣ አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጥቃት የሚፈጸምባቸው፣ በረሃብ የሚሰቃዩ እና ሌሎችም በደሎች ይደርስባቸዋል። ከእነዚህ መካከልም በተለይ ኦማን ውስጥ በሚገኙ አፍሪካውያን የቤት ሠራተኞች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በተመለከተ ቢቢሲ የምርመራ ዘገባ ሠርቷል።
ዓለም የዘነጋቸው እስካሁን አድራሻቸው የማይታወቀው የቺቦክ ሴቶች
በአውሮፓውያኑ ሚያዚያ 2014 276 ሴት ታዳጊዎች ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ ዓለም አቀፍ ታዋቂነት ያላቸው ሰዎች ሳይቀሩ #bringbackourgirls የተሰኘው የማሕበራዊ ሚድያ ዘመቻ ጀመሩ።
በተለያየ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ልጆቻችንን ስለ አደጋዎች እንዴት ማስተማር እንችላለን?
ዕድሜ ሲጨምር ስለ አደጋ ያለ ግንዛቤም ያድጋል። ልጆች ግን ሊገጥማቸው የሚችለውን አደጋ ባለማወቅ በቀላሉ ለጉዳት ሊዳረጉ ይችላሉ። ታዲያ ልጆችን ስለ አደጋ እና ቅድመ ጥንቃቄ ማስተማር የሚቻለው እንዴት ነው? በተለያየ ዕድሜ ላይ ያሉ ልጆችን ስለ አደጋ ማስተማር የሚቻልባቸው መንገዶች አሉ።
100 ዓመት የደፈኑ የዕድሜ ባለፀጋዎች የሚጋሯቸው 8 ሥነ-ልቦናዊ ባህሪያት
አብዛኛዎቹ 100 ዓመት የደፈኑ የዕድሜ ባለፀጋዎች አሁንም ጤናማ ናቸው፤ ጥንካሬያቸው ያስቀናል፤ ከሰው ለማውራት ጉጉ ናቸው። በእንግሊዝኛው ሴንቴናሪያንስ ይባላሉ። 100 ዓመት ያለፋቸው የዕድሜ ባለፀጋዎች ናቸው። እነዚህ የዕድሜ ባለፀጎች የሚያመሳስሏቸው በርካታ የጋራ ባህሪያት አላቸው።
አጃኢብ!
የኢትዮጵያ እና ኬንያ አትሌቶች ሆን ብለው ቻይናዊ ሯጭ እንዲያሸንፍ በማድረግ ተከሰሱ
አንድ የኢትዮጵያ እና ሁለት ኬንያውያን አትሌቶች ቻይናዊ ሯጭ የቤይጂንግ ግማሽ ማራቶንን እንዲያሸንፍ አድርገዋል ተብለው ምርመራ ተጀመረባቸው።
ባለፉት ዓመታት በእስራኤል ከተገደሉ የኢራን ተመራማሪዎች እና የጦር መኮንኖች ዋነኞቹ
እስራኤል ጠላቶቼ ከምትላቸው መካከል በቀዳሚነት ትጠቀሳለች - ኢራን። ኢራንም ብትሆን ‘አጥፊዬ’ ከምትላቸው አገራት መካከል ቀን ከሌት በዐይነ ቁራኛ የምትጠብቃት እስራኤልን ነው። እስራኤል ባለፉት ዓመታት ጥቂት የማይባሉ የኢራን የኑክሌር ሳይንቲስቶችን እና የጦር ጄኔራሎችን ኢላማ አድርጋለች።
በአንድ ጨዋታ 31 ግቦች የተቆጠሩበት ግብ ጠባቂ
በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ሁሉም ተሰላላፊዎች ለቡድኑ ድል እና ሽንፈት ኃላፊነት ቢኖርባቸውም፣ የግብ ጠባቂን ያህል ግን የጎላ አይሆንም። በተለይ ደግሞ አንድ ቡድን በርካታ ግቦች ተቆጥረውበት ሲሸነፍ የሁሉም ዐይን የሚያርፈው በረኛ ላይ ነው። ታዲያ በአንድ ጨዋታ ከሦስት አስሮች በላይ ጎለረ ያስተናገደ በረኛ ምን ይሰማው ይሆን?
ኢራን በበርካታ ግጭቶች ውስጥ ለምን ትሳተፋለች?
እስራኤል በጋዛ እያካሄደችው ያለው የማያባራ ጥቃት በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት በቀጣናው ሌላኛው እየተነሳች ያለች አገር ኢራን ናት። ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ እየተጫወተችው ያለው ሚና የዓለምን ቀልብ እየሳበ ይገኛል።
አሰቃቂው ታሪክ በጥንቃቄ የተቀመጠበት የሩዋንዳው ጄኖሳይድ ሙዚየም በኢትዮጵያዊ ዐይን
በጥቂት ወራት ውስጥ 800 ሺህ ሩዋንዳውያን የተጨፈጸፉበት ዘር ማጥፋት ከተፈጸመ ሦስት አስርት ዓመታት ሆነው። የጎሳ ምንነትን በመለየት በተፈጸመው የዘር ፍጅት አብዛኞቹ ሁቱዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። ሩዋንዳ ይህንን ክስተት ለመዘከር ትልቅ ሙዚየም ገንብታ ታሪኩን ታስታውሳለች። የቢቢሲው ዘጋቢ ውስጥን በሐዘን የሚንጠውን ሙዚየምን ጎብኝቶ የጭፍጨፋውን 30ኛ ዓመትን የሚዘክር ዘገባ አዘጋጅቷል።
ከ156 ዓመታት በፊት የተዘረፉት የአፄ ቴዎድሮስ አልባሳት የት ነው ያሉት?
አንድ የታሪክ ተመራማሪ ከ156 ዓመታት በፊት የተዘረፉት የኢትዮጵያው ንጉሥ አልባሳት የት እንዳሉ ለማወቅ እየጣሩ ነው። ተመራማሪው እነዚህ አልባሳት በእንግሊዝ ማንቸስተር እንደሚገኙ እምነት አላቸው።
አውሮፕላን አብራሪዎች ለረጅም ሰዓታት ነቅተው ለማብረር መድኃኒት ይወስዳሉ?
በቅርቡ የኢንዶኔዢያ አውሮፕላን ዋና እና ረዳት አብራሪዎች በበረራ ላይ ሳሉ እንቅልፍ ጥሏቸዋል መባሉ መነጋገሪያ ሆነዋል። በተለይ ለረጅም ሰዓታት በሚጓዙ አብራሪዎች ላይ ድካም እና መሰላቸት መከሰቱ አይቀርም። ታዲያአብራሪዎች ይህንን ለመቋቋም በሰላም ወደ ማረፊያቸው ለመድረስ ለረጅም ሰዓታት ነቅተው ለማብረር መድኃኒት ይወስዳሉ?
በገዛ ጓደኛዋ ፎቶዋ በረቀቀ ሁኔታ ተቀናብሮ የወሲብ ቪዲዮዎች ድረ-ገጽ ላይ የወጣባት ወጣት
በ20ዎቹ የእድሜዋ አጋማሽ ላይ የምትገኘው ጆዲ ለጠላቷ የማትመኘው ነገር ገጥሟታል። ፎቶግራፏ የእውነት በሚመስል ሁኔታ ተቀነባብሮ ልቅ የወሲብ ፊልሞች በሚታዩባቸው ድረ-ገጾች ላይ ምሥሏ ተሠራጭቶ አግኝታዋለች። ከዚህ እኩይ ተግባር ጀርባ ያለው ደግሞ የቅርቤ የምትለው ጓደኛዋ መሆኑ ጉዳቷን የከፋ አድርጎታል።
የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ፆታ መቀየርና የማሕፀን ኪራይን በተመለከተ ያላትን አቋም እንደማትቀይር ይፋ አደረገች
ፅሑፉ ሌሎች እንደ ድኅነት፣ ስደት እና ሕገ-ወጥ የሰው ልጅ ዝውውር ያሉ ማሕበራዊ ጉዳዮችንም አንስቶ የሰው ልጅ ክብርን የሚገረስሱ ናቸው ይላል። መግለጫውን በፊርማቸው ያፀደቁት ሊቀ-ጳጳስ ፍራንሲስ ናቸው።
ልብሳችን ወልቆ ተፈትሸናል ሲሉ ኳታር አየር መንገድን የከሰሱ ሴቶች መዝገብ ውድቅ ሆነ
በአውሮፓውያኑ 2020 ሐማድ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ውስጥ ሕፃን ልጅ ያለጠባቂ መገኘቱን ተከትሎ ነበር አየር መንገዱ ክስ ያቀረቡትን እና የሌሎች ሴት መንገደኞችን ልብስ አስወልቆ የፈተሸው።
‘እውነት ሰውነቷ አጥንት አለው?’ ተብላ የተደነቀችው የሰርከስ ባለሙያ ሰናይት
“ሰርከስ ዓለሜ፣ ሕይወቴ ነው” የምትለው ሰናይት አሰፋ ብሪታንያ የምትኖረው ሲሆን በአሜሪካ፣ ስፔን፣ ስዊትዘርላንድ፣ ዱባይ፣ ቻይና፣ ጀርመን፣ ሩሜንያ፣ ቤላሩስ እና አውስትራሊያ ላይ ባሳየችው ትርዒት መድረክ ላይ ኮከብ ሆና ለመድመቅ በቅታለች። በምታሳያቸው ትርዒቶች የተነሳም በሰውነቷ ውስጥ አጥንት አለ ወይ የሚል ጥያቄን ፈጥሯል።
ፍሪጅ አል መረር፡ የኢትዮጵያውያን “ቡና ቤቶች” በዱባይ
በርካታ ኢትዮጵያውያን ከሚኖሩባቸው የባሕረ ሰላጤው አረብ አገራት መካከል ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ቀዳሚዋ ሳትሆን አትቀርም። በአገሪቱ ውስጥም ብዙ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የሥራ መስኮች ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ። አንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ በተለይ ኢትዮጵያውያን የዕለት ከዕለት ሥራቸውን ለማከናወን እና ኑሯቸውን ለመግፋት የሚያዘወትሯቸው ናቸው። የዱባዩ ፍሪጅ አል መረር የሚባለው አካባቢ ደግሞ የኢትዮጵያውያን የሥራ ቦታ ከመሆን አልፎ የኢትዮጵያን ገጽታ የተላበሰ ነው።
የተመለሱ ጥያቄዎች
የኢድ አል-ፈጥር በዓል ቀን የሚወሰነው እንዴት ነው?
1445ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል ዛሬ ረቡዕ ሚያዚያ 2/2016 በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ቅዱስ የሆነው የረመዳው ወር ሲጠናቀቅ ከፍ ያለ ሃይማኖታዊ ትርጉም የሚሰጠው የኢድ-አልፈጥር በዓል ይከበራል።
የአእምሮ ጤና እክል የሆነው ባይፖላር ዲስኦርደር ምንድን ነው? ለምንስ ከታዋቂው ሠዓሊ ጋር ተያያዘ?
በተቃራኒ የስሜት ጽንፎች ውስጥ መዋለል (ባይፖላር ዲስኦርደር) ከ100 ሰዎች ውስጥ በአንድ ሰው ላይ ይከሰታል። ስለዚህ የአእምሮ ጤና እክል ግንዛቤን ለማስፋት መጋቢት 21 በየዓመቱ የባይፖላር ዲስኦርደር ቀን ይታሰባል። ይህ ቀን ደግሞ የታዋቂው ሠዓሊ ቪንሰንት ቫን ጎ የልደት ቀን ነው። ዕለቱ ለምን ከእሱ ጋር ተያያዘ? ቫን ጎ ባይፖላር የአእምሮ ጤና ችግር ነበረበት?
የአሜሪካን ገመና ለዓለም ይፋ ያደረገው ጁሊያን አሳንጅ ማን ነው?
የአሜሪካን ገመና ለዓለም ይፋ ያደረገው ዊክሊክስ የተሰኘው ድረ ገጽ መሥራች ጁሊያን አሳንጅ ከሰሞኑ የበርካታ መገናኛ ብዙኃን ዋነኛ ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል።
ችላ ተብለው በአሳሳቢ ደረጃ በመላው ዓለም እየተስፋፉ የመጡት የአባላዘር በሽታዎች
እንደ የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ በመላው ዓለም በየቀኑ ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች በግብረ ሥጋ ግንኙነት በሚተላለፉ በሽታዎች ይያዛሉ። ነገር ግን በትክክል በወሲብ የሚተላለፍ በሽታ ምንድን ነው? ዓይነቶቹ እና ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው? ራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን?
ማንኮራፋት እንዴት ትዳርን እስከ ማፍረስ ሊያደርስ ይችላል? ምንስ መፍትሄ አለው?
የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ለሚያንኮራፋው እና ከጎን ለሚተኛ አካላዊ እና የአእምሮ ጤና ጉዳት ያስከትላል። ትዳር ሊያፈርስ ይችላል።
ፆም በሰውነታችን ውስጥ የሚያስከትለው ለውጥ እና የሚሰጠው ጥቅም ምንድን ነው?
ለእስልምና እና ለክርስትና እመነት ተከታዮች ዋነኞቹ የፆም ወቅት የሆኑት ረመዳን እና ዓቢይ ፆሞች ተጀምረዋል። የሁለቱም እምነቶነቶች ምዕመናን የፆሙን ጊዜ በየራሳቸው ሥርዓት እና ደንብ መሠረት የሚከውኑት ሲሆን፣ በየዕለቱ ለረጅም ሰዓታት ከምግብ እና ከውሃ ርቀው ይቆያሉ። በዚህ ጊዜ ታዲያ ፆም በሰውነት ላይ ምን ለውጥን ያስከትላል? ምንስ ጥቅም አለው?
በረመዳን የፆም ወቅት የትኞቹን ዓይነት ምግቦች መመገብ፣ የትኞቹንስ መተው አለብን?
ረመዳን የፆም ወቅት ሙስሊሞች በጉጉት የሚጠብቁት ጊዜ ነው። ከማለዳ ጀምሮ አስከ ምሽት ድረስ ምግብ ሳይቀመስ የሚቆይበት የፆም ጊዜ የመጀመሪያ ቀናት ለአንዳንዶች ፈታኝ ነው። በፆሙ ወቅት መደበኛ እንቅስቃሴያችንን እያደረግን ያለድካም ለመቆየት የሚያስችሉ ዘዴዎችን የሥነ ምግብ ባለሙያዎች ይመክራሉ። በዚህ ወቅት ምን ዓይነት ምግቦችን መመገብ፤ የትኞችንስ ማስቀረት አለብን?
ራስን ማጥፋት የሚያበረታታው እና ለበርካቶች ሞት ምክንያት የሆነው መርዝ ሻጭ በቢቢሲ ተጋለጠ
በዩናይትድ ኪንግደም ቢያንስ 130 ሰዎች ራሳቸውን አጥፍተውበታል የተባለውን መርዝ የሸጠውን ዩክሬናዊ ቢቢሲ ተከታትሎ ደርሶበታል። ሊዮኒድ ዛኩተንኮ የተባለው ይህ ግለሰብ ራስ ማጥፋትን የሚያበረታታበት እንዲሁም አገልግሎቱን የሚያስተዋውቅበት ድረ ገጽ አለው።
ማር ለጤናችን ምን ያህል ጠቃሚ ነው? መመገብ ያለባቸውስ እነማን ናቸው?
ከስኳር የሚጣፍጠው የተፈጥሮ ማር ብቸኛው የስኳር አማራጭ ነው? ለሁሉም ሰውስ በእኩል ይጠቅማል? ሕጻናትን ለመመገብስ የዕድሜ ገደብ አለው? የምንወስደው መጠንስ ምን ያህል መሆን አለበት? ለእነዚህ የበርካታ ሰዎች የዘውትር ጥያቄዎች የሥነ ምግብ ባለሙያ የሆኑት ጆ ልዊን ምላሽ አላቸው።
የተጠጋገኑ እና ኦሪጂናል ያልሆኑ የሞባይል ቻርጀሮች እኛንም ስልካችንንም እንደሚጎዱ ያውቃሉ?
ሊበጠስ ጫፍ የደረሰ እና የተጠጋገነ የሞባይል ቻርጅ ማድረጊያን መጠቀም ብዙዎቻችን ምንም ጉዳት የሌለው ይመስለናል። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ያልተጠበቀ ሲከፋም አሰቃቂ አደጋን ሊያስከትል ይችላል። በጥሩ ሁኔታ ላይ ያልሆኑ የሞባይል ቻርጀሮችን መጠቀም ምን ችግርን ሊያስከትሉ ይችላሉ? ምን ዓይነት ቻርጀሮችን ብንጠቀም ይመከራል?
ደም ግፊትን ዝቅ ማድረግን ጨምሮ ቀይ ሥር የሚሰጣቸው አምስት ጥቅሞች
የቀይ ሥርን ለየት ያለ ጠቅምን በተመለከተ የሥነ ምግብ እና የጤና ባለሙያዎች መረጃዎችን እያጋሩ ሲሆን፣ በዕለት ከዕለት ምግባችን ውስጥም ቀይ ሥርን እንድናካትት እየመከሩ ነው። ቀይ ሥር የደም ግፊትን እንዴት ሊቀንስ ይችላል? እንዴትስ ነው መመገብ ያለብን?
“የልጆቼን ሳቅ መስማት ለእኔ ስቃይ ነው”
የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ የጤና አገልግሎት (ኤንኤችኤስ) ድረ ገጹ ላይ ባሰፈረው መረጃ አንድ ሰው በየቀኑ የሚሰማቸው ድምጾች በትክክል ከሆኑት በላይ ከፍ ብለው ከተሰሙት ሃይፐራኪዩሲስ ሊኖርበት ይችላል። ድምጹ ከፍ ብሎ ከመሰማቱ ባሻገርም አንዳንዴ ህመም ሊያስከትል ይችላል።