BBC News, አማርኛ - ዜና
BBC News Amharic Top Stories
ከ20 በላይ ኢትዮጵያውያን የሞቱበት የጀልባ አደጋ የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በስደተኛው አንደበት
ሰኞ ሚያዝያ 14/2016 ዓ.ም. የመን ውስጥ በስደት ሲንከራተቱ ቆይተው ወደ አገራቸው ለመመለስ የተነሱ ሰባ ሰባት ኢትዮጵያውያንን አሳፍራ ወደ ጂቡቲ ያቀናችው ጀልባ ወደ ባሕር ዳርቻው ብትቃረብም በሰላም ካሰበችበት አልደረሰችም። በገጠማት የመገልበጥ አደጋ ከ20 በላይ ኢትዮጵያውያን ባሕር ላይ ቀርተዋል። ከአደጋው የተረፈ አንድ ኢትዮጵያዊ አደጋው እንዴት እንደተከሰተ ለቢቢሲ ተናግሯል።
አፍሪካን በሩጫ ለማቋረጥ የተነሳው ግለሰብ በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት “ሕልሜ ሊከስም” ነው አለ
አህጉረ አፍሪካን በፍጥነት በሩጫ በማቋረጥ ክብረ-ወሰን ለመስበር ያለመው ግለሰብ በደኅንነት ስጋት ምክንያት ዕቅዱ ሊከስምበት እንደሆነ ተናግሯል።
ጣልያን ለኢትዮጵያውያን ስደተኞች ምን ያህል ምቹ ናት?
በዕድሉ መንገሻ እና አበባ ተስፋዬ በተለያየ ጊዜ ከሱዳን ተነስተው፣ የሊቢያ በርሃን አቆራርጠው፣ የሜድትራኒያንን ባህር ሰንጥቀው ነበር ጣልያን የደረሱት። በዚያ ጉዞ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለው ፈተናን አይተዋል። ጭው ባለ በርሃ የሰው ልጆችን የሰውነት ቅሪት እየተመለከቱ፣ እየተደበደቡ፣ እየተራቡ፣ እየተጠሙ እና በህይወታቸው ‘እየቆመሩ’ የተመኟትን ጣልያን ከረገጡ ዓመታትን አስቆጥረዋል። ተስፋ ያደረጓት ጣልያን እንዴት ተቀበለቻቸው? ጣልያን ለኢትዮጵያን ስደተኞች ምን ያህል ምቹ ናት? የቢቢሲ ጋዜጠኞች ጣልያን በሄዱበት ወቅት ታሪካቸውን አጋርተዋል።
ቀሲስ በላይ መኮንን፤ በሐሰተኛ ሰነድ ገንዘብ ለማውጣት በተሞከረበት ቦታ የተገኙት “ሰዎች አታለዋቸው” መሆኑን ተናገሩ
ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማውጣት በመሞከር የተጠረጠሩት ቀሲስ በላይ መኮንን፤ ድርጊቱ በተፈጸመበት ቦታ የተገኙት “ሰዎች አታልለዋቸው” እንደሆነ ለፍርድ ቤት መግለጻቸውን ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ለቢቢሲ ተናገሩ።
በኬንያ ናይሮቢ በተከሰተ ከባድ ጎርፍ ቢያንስ 32 ሰዎች ሞቱ
በኬንያ መዲና ናይሮቢ በተከሰተ ከባድ ጎርፍ መንገዶች በውሃ ተጥለቅልቀው የታዩ ሲሆን የሀገሪቱ ባለስልጣን የጎርፉ መጠን “እጅግ በከፋ ደረጃ እየጨመረ ነው” ብለዋል።
ስለ ክትባት ያልተረጋገጡ የሴራ ትንተናዎችን የሚያሠራጩት ተጽእኖ ፈጣሪ ፓስተር
“ክራይስት ኤምባሲ” የተባለው ቤተክርስቲያን መሥራች እና መሪ የሆኑት ናይጄሪያዊው ፓስተር ክሪስ ኦያኪሂሎሜ በስብከታቸው ውስጥ የሚያስተላልፉት መልዕክት ላይ ክስ ይቀርብባቸዋል። በተለይ በክትባት ዙሪያ የሚያሠራጩት የሴራ ትንተና በተለያዩ የአፍሪካ አገራት የሚገኙ ተከታዮቻቸውን ጤና አደጋ ላይ የሚጥል ነው እየተባለ ነው። ፓስተሩ ምን አሉ?
አንዳንድ አገራት ፍልስጤምን እንደ አገር ዕውቅና የማይሰጧት ለምንድነው?
ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ፍልስጤም የድርጅቱ ሙሉ አባል ለመሆን ባቀረበችው ጥያቄ ላይ ድምፅ ሰጥቷል። ዩናይትድ ስቴትስ ድምፅን በድምፅ የመሻር ሥልጣኗን ተጠቅማ ይህን ጥያቄ ውድቅ ብታደርገውም 12 የምክር ቤቱ አባላት ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። ነገር ግን የአገርነት ጥያቄዋ ተቀባይነት አላገኘም። አንዳንድ አገራት ለፍልስጤም የአገርነት ዕውቅና ለምን ይነፍጓታል?
በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ድንኳኖችን የዘረጉት የፍልስጤም ደጋፊዎች በተቃውሟችን እንቀጥላለን አሉ
በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ ለአንድ ሳምንት ያህል ድንኳኖችን ተክለው በፍልስጤማውያን ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት እየተቃወሙ ያሉ ተማሪዎች በተቃውሟቸው እንደሚቀጥሉ ተናገሩ።
የኢራን መንግሥትን የተቃወመው ራፐር ሞት እንደተፈረደበት ጠበቃው ተናገረ
መንግሥትን የሚቃወሙ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ የታሰረው ኢራናዊ ራፐር በሞት እንዲቀጣ በፍርድ ቤት ውሳኔ መተላለፉን ጠበቃው ገለጸ።
የመንገዶች አስተዳደር በተቋረጡ እና በቆሙ የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይ የ35 ቢሊዮን ብር ካሳ በተቋራጮች ተጠየቀ
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር “በፀጥታ ችግር” ምክንያት በተቋረጡ እና በቆሙ የመንገዶች ፕሮጀክቶች ላይ 34.95 ቢሊዮን ብር ካሳ በተቋራጮች መጠየቁን አስታወቀ። አስተዳደሩ እስከ 2016 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ድረስ “በፀጥታ ችግር” ምክንያት “ሙሉ በሙሉ የኮንትራት ውላቸው የተቋረጠ” 31 የመንገድ ፕሮጀክቶች መኖራቸውንም ይፋ አድርጓል።
አቶ ጌታቸው ረዳ ከብልፅግና ጋር ስለመዋሃድ፣ ስለሰሞኑ ግጭት እና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ስላላቸው ግንኙነት ምን አሉ?
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ህወሓትን ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ስለማዋሃድ፣ ስለሰሞኑ ግጭት፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ስላለቸው ግንኙነት እና የይገባኛል ጥያቄ ስለሚነሱባቸው አካባቢዎች ለቢቢሲ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በአዲስ አበባ የግንባታ ድንጋይ እና አፈር ተደርምሶ የ4 ዓመት ህጻንን ጨምሮ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ስሙ ጠሮ መስጂድ በተባለ አካባቢ ለቤት ግንባታ የተከመረ ድንጋይ እና አፈር ተንዶ የሰባት ሠዎች ሕይወት አለፈ።
አነጋጋሪ ጉዳይ
የብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ አባላት በሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት እና አሳሳች የፌስቡክ ዘመቻዎች ላይ መሳተፋቸውን የቢቢሲ ምርመራ አረጋገጠ
በገዢው ብልፅግና ፓርቲ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስር የሚንቀሳቀሱ እና ‘የሚዲያ ሠራዊት’ የሚል መጠሪያ ያላቸው የፓርቲው አባላት፤ መንግሥትን በሚተቹ እና በሚቃወሙ ግለሰቦች ላይ በፌስቡክ በተደረጉ የሐሰተኛ መረጃ እና በተቀናጁ ዘመቻዎች ላይ እንደተሳተፉ ቢቢሲ ያደረገው ምርመራ አረጋገጠ።
ከሶማሊያ ጋር ወታደራዊ ስምምነት የደረሰችው የቱርክ የጦር መርከብ ሞቃዲሾ ወደብ ደረሰች
ከጥቂት ወራት በፊት በሶማሊያ እና በቱርክ መካከል የተደረሰውን የወታደራዊ ትብብር ስምምነትን ተከትሎ የቱርክ ባሕር ኃይል የጦር መርከብ ሞቃዲሾ ወደብ ደረሰች።
በሁለት ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በደረሰ የጀልባ አደጋ 21 ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ሞቱ
በሁለት ሳምንት ልዩነት ውስጥ ዳግም ቀይ ባሕር ላይ ባጋጠመ የጀልባ መስመጥ አደጋ የ21 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ።
በደቡብ ጎንደር አምስት ሰዎች ሲገደሉ 18 ቤቶች መቃጠላቸውን ተጎጂዎች እና የዐይን እማኞች ተናገሩ
በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ አጎና በተባለ ‘የቀበሌ ከተማ’ ባለፈው ሰኞ ሚያዚያ 7/2016 ዓ.ም. በፋኖ እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል የተካሄደ ግጭትን ተከትሎ ነዋሪዎች መገደላቸውን እና በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን የተጎጂ ቤተሰቦች እና የዐይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ዩኬ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የምትልክበት ሕግ ምንድን ነው? ተፈጻሚነቱስ በማን ላይ ነው?
ለበርካታ ወራት ብዙ ሲያወዛግብ የቆየው ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የሚልከው ሕግ በዩናይትድ ኪንግደም ፓርላማ ጸድቆ ሕግ ሆኗል። ይህ ሕግ ምን አካቷል? የትኞቹንስ ስደተኞች ይመለከታል?
ዩክሬን እና ሩሲያ ሱዳን ውስጥ በእጅ አዙር ጦርነት እያካሄዱ ነው?
መስከረም 2016 ዓ.ም. ላይ በማይገመት ቦታ፣ ጨርሶ ሊገመቱ በማይችሉ ሁለት መሪዎች መካከል ስብሰባ ተደረገ። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቭሎድሚር ዜሌንስኪ ከሱዳኑ መሪ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን ጋር በአየርላንድ በሚገኝ አየር ማረፊያ መገናኘታቸው ብዙዎችን አስደንቆ ነበር።
የኢትዮጵያውያን ስደተኞች መዳረሻ የሆነችው ደቡብ አፍሪካ ያቀደችው የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ምን ይዟል?
የበርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መዳረሻ የሆነቸው ደቡብ አፍሪካ እየሠራችበት ያለውን ‘የቅኝ ግዛት’ የኢሚግሬሽን ሥርዓት ልታሻሽል መሆኑን አስታውቃለች። የደቡብ አፍሪካ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር የአገሪቱ የኢሚግሬሽን ሕግጋት ጠበቅ ያሉ እንዲሆኑ እና የዜግነት እንዲሁም የጥገኝነት ሂደቶችን የሚያሻሽለውን አዲሱን ዕቅድ ይፋ አድርገዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ታዳጊዎችን ጨምሮ አራት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን፤ “ከምዕራብ ጉጂ ዞን መጥተዋል” የተባሉ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ሦስት ታዳጊ ልጆችን ጨምሮ አራት ሰዎች መገደላቸውን ጥቃቱ የተፈጸመበት ቆቦ ቀበሌ ሊቀመንበር እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ከአላማጣ እና የራያ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 50 ሺህ መድረሱን ተመድ አስታወቀ
ግጭት በተነሳባቸው የአላማጣ ከተማ፣ ዛታ እና ኦፍላ የራያ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 50 ሺህ መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ተፈናቃዮቹ የተጠለሉባቸውን የዞን ባለስልጣናት ዋቢ አድርጎ ጽህፈት ቤቱ ሚያዝያ 14/2016 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት 42 ሺህ የሚሆኑ ተፈናቃዮች በሰሜን ወሎ ቆቦ ከተማ እንዲሁም 8300 የሚሆኑት ደግሞ በሰቆጣ እና ዋግ ኽምራ ዞኖች ተጠልለዋል ብሏል።
በዓለም ላይ ግዙፍ ገደሎች የመኖርያ መንደሮችን እየዋጡ ነው
የአየር ንብረት ለውጥ ለሸለቆዎች መሸርሸር ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ከፍተኛ የዝናብ መጠን እንዲኖር በማድረግ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል።
አባ ገዳ ጎበና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባል የሆነው ልጃቸው መገደሉን ከማኅበራዊ ሚዲያ መስማታቸውን ተናገሩ
የቱለማ አባ ገዳ የሆኑት አባ ገዳ ጎበና ሆላ ኢሬሶ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባል የሆነው ልጃቸው መገደሉን ከማኅበራዊ ሚዲያ መስማታቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።
የውጭ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ከወጪ እስከ ችርቻሮ ንግድ ዘርፍ መግባታቸው በረከት ወይስ ስጋት?
ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ለውጭ ባለሃብቶች ዝግ ሆነው የኖሩ የምጣኔ ሃበት ዘርፎችን እየከፈተች ነው። በቅርቡ ድግሞ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ተጠብቀው የነበሩት የወጪ፣ የገቢ፣ የጅምላ እና የችርቻሮ ንግድ ዘርፎች ክፍት እንዲሆኑ ተወስኗል። ይህ ውሳኔ የአገር ውስጥ ባላሃብቶችን እና ነጋዴዎችን ከገበያ ያስወጣል የሚሉ እንዳሉ ሁሉ፤ ውድድርን በመፍጠር ለሸማቾች አማራጮችን ያቀርባል የሚሉ አሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ምን ይላሉ?
ከየፈርጁ
እስራኤል እና ኢራን ጦርነት ውስጥ ቢገቡ ምን ይከሰታል? በወታደራዊ አቅምስ ይመጣጠናሉ?
ኢራን እና እስራኤል እስካለፈው ሳምንት ድረስ በእጅ አዙር እንጂ በቀጥታ ግጭት ውስጥ ገብተው አየውቁም። አሁን ግን በሚሳኤል እና በድሮኖች አንደኛው በሌላኛው ላይ ግልጽ ጥቃት መፈጸም ጀምረዋል። ለመሆኑ እስራኤል እና ኢራን ጦርነት ውስጥ ቢገቡ ምን ሊከሰት ይችላል? ሁለቱ አገራትስ በወታደራዊ አቅም ምን ያህል ይመጣጠናሉ?
ኢትዮጵያ፡ 56 በመቶ የሚሆኑ የሁለተኛ እና ሦስተኛ ክፍል ተማሪዎች ፊደል መለየት እንደማይችሉ ጥናት አመለከተ
በኢትዮጵያ ከሚገኙ የሁለተኛ እና ሶስተኛ ክፍል ተማሪች 56 በመቶዎቹ ምንም ዓይነት ቃል ማንበብ እንደማይችሉ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባደረገው ጥናት አመልክቷል። አገልግሎቱ በጥናቱ ተሳተፊ ካደረጋቸው የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ቢያንስ አንድ ቃል ማንበብ የሚችሉ 37 በመቶ የሚሆኑት ብቻ እንደሆኑ በአገልግሎቱ የትምህርት ምዘናና ምርምር መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤፋ ጉርሙ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ገልጸዋል። የተቀሩት 63 በመቶዎቹ አንድም ቃል ማንብብ የማይችሉ (Zero renderers) ናቸው።
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ ለአምስት ዓመታት ከአትሌቲክስ ታገደች
የ21 ዓመቷ የመካከለኛ ርቀት አትሌት ለአምስት ዓመታት መታገዷን የገለጠው አትሌቲክስ ኢንቴግሪቲ ዩኒት የተባለው ተቋም ነው። ተቋሙ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹላ በለጠፈው መግለጫ አትሌቷ ምርመራ ከተደረገላት በኋላ ቅጣት ማስተላለፉን አሳውቋል።
ረሃብ ባንዣበበባት ሱዳን ከጦርነቱ ከሚሸሹ ሰዎች የሚሰሙ የግድያ እና የመደፈር ታሪኮች
አንድ ዓመት ያለፈው የሱዳን የእስር በርስ ጦርነት እንደቀጠለ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የገደለው ጦርነት ሚሊዮኖችን አፈናቅሏል። ፤ሎች ሚሊዮኖች ደግሞ በረሃብ አፋፍ ላይ ከሚገኙባት ሱዳን ዘግናኝ የግድያ እና ፆታዊ ጥቃት ታሪኮች እየተሰሙ ነው።
ኢራን እና እስራኤል ለምን ደመኛ ጠላቶች ሆኑ?
ኢራን ከግብፅ ቀጥላ ለእስራኤል እውቅና በመስጠት ሁለተኛዋ እስላመዊ አገር ነበረች። ነገር ግን ከኢራን እስላማዊ አብዮት በኋላ ይህ ግንኙነት ተበላሽቶ ከአምስት አስርታት በላይ በጠላትነት እየተያዩ ቆይተዋል። ለመሆኑ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ወደ ደመኛ ጠላትነት ለምን ተሸጋገረ?
ቪዲዮ, አንድ ዓመት በሞላው ጦርነት ለውስብስብ ችግር የተጋለጡት ሱዳናውያን ክርስቲያኖችርዝመት, 1,54
ባለፈው ዓመት የተቀሰቀሰው የሱዳን ጦርነት ክርስቲያኖችን አጣብቂኝ ውስጥ ከቷቸዋል። በጦርነቱ መጀመሪያ አካባቢ ክርስቲያኖች በተለየ መልኩ ተጠቅተዋል የሚሉ መረጃዎች ሲወጡ ነበር። አብያተ ክርስቲያናት ተዘርፈዋል፤ አንዳንዶቹም በከባድ መሣሪያ ጥቃት ደርሶባቸዋል። ከአንድ ዓመት በኋላ ብዙዎቹ ወደ ግብፅ ሲሰደዱ፣ ቀሪዎቹም ተጠልለው ከሚገኙበት ፖርት ሱዳን ለመሰደድ አማራጮችን እየፈለጉ ነው።
ቪዲዮ, ምንጩ ከኢትዮጵያ የሆነው ቡና ለጤና እና ለዓለም ሥልጣኔ ስላበረከተው አስተዋጽኦ በጥቂቱርዝመት, 6,19
በዓለም ላይ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በየዕለቱ ቡና ይጠጣሉ። ቡና ቢያንስ ላለፉት 1500 ዓመታት እንደተጠጣ ይነገራል። ምንጩ ከኢትዮጵያ የሆነው ይህ ፍሬ ዛሬ ዓለም ላለችበት ዕድገትም የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል በማለት ምሁራን ይጠቅሱታል። በሌላ በኩል በሰውነታችን ውስጥ የተለያዩ በሽታዎችን በመከላከልና አዕምሮን በማንቃት አስተዋጽኦ እንዳለው የጤና ሙያተኞች ይመሰክራሉ። ቢቢሲ በዚህ ቪዲዮ ስለቡና ታሪካዊ ዳራ፣ ጠቀሜታዎች እና የጎንዮሽ ጉዳቶች በአጭሩ አቅርቧል።
ከ50 በላይ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ስደተኞች በሱዳን ኃይሎች እንደምርኮኛ መያዛቸው ተነገረ
በሱዳን በኩል ወደ ሊቢያ ለማቋረጥ ሲሞክሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ወጣት ስደተኞች ለአንድ ዓመት በቆየው የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ በሚገኙ ተዋጊ ኃይሎች እንደ ምርኮኛ ተይዘው እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ።
በዩናይትድ ኪንግደም የጥገኝነት ጠያቂዎች ሆቴል ውስጥ የምትኖረው የብስክሌት ሻምፒዮኗ ትርሐስ
በኢትዮጵያ የብስክሌት ሻምፒዮናዋ ትርሐስ ተስፋይ በለንደን ትልቁ የብስክሌት ውድድር ለመሳተፍ በዝግጅት ላይ ናት። ትርሐስ ለስደት ተዳርጋ በምዕራብ ለንደን ጥገኝነት ጠያቂዎች በሚኖሩበት ሆቴል ውስጥ ነው የምትኖረው።
ወደ ባንኮች ያዘዋወሩትን ገንዘብ መመለስ ባለመቻላቸው አጣብቂኝ ውስጥ የገቡት ተማሪዎች
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በገንዘብ ዝውውር ሥርዓቱ ላይ አጋጥሞት በነበረው ችግር ምክንያት በርካታ ደንበኞቹ የራሳቸው ያልሆነ የገንዘብ መውሰዳችን አሳውቆ አብዛኛውን ገንዘብ ማስመለሱንም መግለጹ ይታወሳል። ያልመለሱትን ደግሞ ፎቷቸውን ጨምሮ መረጃቸውን በተለያየ መንገድ ይፋ አድርጓል። በዚህ ጉዳይ ውስጥ ስማቸው በስፋት ሲነሳ የነበሩ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መውደቃቸውን እየተናገሩ ነው።
ታዋቂው ደራሲ ሳልማን ሩሽዲ በስለት ተወግተው ዐይናቸውን ያጡባትን ዕለት ሲያስታውሱ
ታዋቂው ደራሲ ሰር ሳልማን ሩሽዲ ከሦስት አስርት ዓመታት በፊት ባሳተሙት መጽሐፋቸው ምክንያት ተደጋጋሚ የግድያ ዛቻ ሲሰነዘርባቸው ቆይተው ከሁለት ዓመት በፊት ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል። በዚህም አንድ ዐይናቸውን ያጡ ሲሆን፣ ያቺን ዕለት ሲያስታውሱ የዐይን ብርሃናቸውን ማጣታቸው ማጣታቸው በእጅጉ እንደሚያንገበግባቸው ይናገራሉ።
አጃኢብ!
በእስራኤል ጥቃት ከተገደለች ፍልስጤማዊት እናት ማህጸን ልጇን ማትረፍ ተቻለ
ፍልስጤማዊቷ ሳብሪን ለወራት ያህል የተሸከመቻትን ህጻን አይኗን ሳታይ እና ሳታቅፍ ተገደለች። የሰባት ወር ተኩል ነፍሰ ጡር ነበረች።
ቪዲዮ, በበርካታ አገራት ከተሞችን በማውደም አሳሳቢ አደጋን እየጋረጠ ያለው የመሬት መንሸራተትርዝመት, 3,44
በዚህ ዘመን የመሬት መንሸራተት በበርካታ የዓለም አካባቢዎች አሳሳቢ እየሆነ የመጣ ክስተት ነው። ባለሙያዎች እንደሚሉት ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። በደቡብ አሜሪካ እና በአፍሪካ የሚገኙ አንዳንድ ከተሞችም ለውድመት ሲዳረጉ፣ በርካታ ሰዎችም ሕይወታቸውን አጥተዋል። የመሬት መሸርሸር ተፈጥሯዊ ቢሆንም ሰው ሰራሽ ምክንያቶች እንዳባባሱት ባለሙያዎች ይገልጻሉ። በዚህም ሳቢያ በአፍሪካ እና በደቡብ አሜሪካ ያሉ ከተሞች አደጋ ተጋርጦባቸዋል።
በቦኮሃራም የታገተችው ናይጄሪያዊት ተማሪ ከ10 ዓመት በኋላ ሦስት ልጆችን ወልዳ ነጻ ወጣች
ከአስር ዓመት በፊት በቦኮሃራም ታጣቂዎች ታግተው ከነበሩ ሴቶች መካከል አንዷ የሦስት ልጆች እናት ሆና በናይጄሪያ መንግሥት ወታደሮች ነጻ ወጣች።
አደገኛ በመሆኑ ከገበያ እንዲሰበሰብ ስለተባለው የህጻናት የሳል ሽሮፕ ምን እናውቃለን?
ቢያንስ አምስት የሚሆኑ የአፍሪካ አገራት የተወሰኑ የጆንሰን ኤንድ ጀንሰን የሳል ሽሮፖች ከገበያ እንዲሰበሰቡ አዘዋል። “እጅግ ከፍተኛ” መርዛማ እና የመግደል አቅም ያለው ዳይትሊን ግላይኮል የተባለውን ንጥረ ነገር በምርመራ እንዳገኙበት ገልጸዋል።
በእስራኤል ጥቃት በአንድ ላይ ስለተገደሉት የሐማስ መሪ ልጆች እና የልጅ ልጆች ምን እናውቃለን?
የሐማስ የፖለቲካ መሪ እስማኤል ሃኒዬህ ሦስት ልጆች እና አራት የልጅ ልጆቻቸው ረቡዕ ዕለት እስራኤል ጋዛ ውስጥ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ተገድለዋል። ለመሆኑ የተገደሉት የሃንዬህ ልጆች በሐማስ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፎ አላቸው?
ቡና እንዴት በዓለማችን በብዙዎች የሚወደድ አነቃቂ ፍሬ ሊሆን ቻለ?
እንቅልፍ ከማትተኛው የኒው ዮርክ ከተማ እስከ ኢትዮጵያ ተራሮች ድረስ ዝናው የናኘ ነው፤ ቡና። ሚሊዮኖች ሳይጎነጩት መዋል አይቻላቸውም። ቡና ለ15 ክፍለ ዘመናት የሰው ልጆች ባህል ማዕከል ሆኖ ኖሯል። አንዳንዶች የ17ኛው እና የ18ኛው ክፍለ ዘመን አብርሆት ከቡና ነው የመነጨው ይላሉ።
ኢትዮጵያ ፆታዊ ጥቃት ፈጻሚዎችን ከሥራ እና ከማኅበራዊ ግልጋሎቶች የሚያገል ምዝገባ ልትጀምር ነው
የኢትዮጵያ መንግሥት ፆታዊ ጥቃት ፈጻሚዎችን የሚመዘግብ ሥርዓት ሊጀምር መሆኑን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። ምዝገባው ፆታን መሠረት አድርገው የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከል እና ለመቀነስ ያለመ ነው የተባለ ሲሆን፣ በተለይ “ወሲባዊ ጥቃቶች ላይ ትኩረት” እንደሚያደርግ ተነግሯል።
100 ዓመት የደፈኑ የዕድሜ ባለፀጋዎች የሚጋሯቸው 8 ሥነ-ልቦናዊ ባህሪያት
አብዛኛዎቹ 100 ዓመት የደፈኑ የዕድሜ ባለፀጋዎች አሁንም ጤናማ ናቸው፤ ጥንካሬያቸው ያስቀናል፤ ከሰው ለማውራት ጉጉ ናቸው። በእንግሊዝኛው ሴንቴናሪያንስ ይባላሉ። 100 ዓመት ያለፋቸው የዕድሜ ባለፀጋዎች ናቸው። እነዚህ የዕድሜ ባለፀጎች የሚያመሳስሏቸው በርካታ የጋራ ባህሪያት አላቸው።
በተለያየ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ልጆቻችንን ስለ አደጋዎች እንዴት ማስተማር እንችላለን?
ዕድሜ ሲጨምር ስለ አደጋ ያለ ግንዛቤም ያድጋል። ልጆች ግን ሊገጥማቸው የሚችለውን አደጋ ባለማወቅ በቀላሉ ለጉዳት ሊዳረጉ ይችላሉ። ታዲያ ልጆችን ስለ አደጋ እና ቅድመ ጥንቃቄ ማስተማር የሚቻለው እንዴት ነው? በተለያየ ዕድሜ ላይ ያሉ ልጆችን ስለ አደጋ ማስተማር የሚቻልባቸው መንገዶች አሉ።
ቪዲዮ, ቢቢሲ ያጋለጠው የአፍሪካውያን የቤት ሠራተኞች ሰቆቃ በባሕረ ሰላጤዋ አገርርዝመት, 5,25
በባሕረ ሰላጤው አገራት ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ የቤት ውስጥ ሠራተኞች ይገኛሉ። ኑሮን ለማቃናት ወደ አረብ አገራቱ ያቀኑት አፍሪካውያን ግን ሥራ እና ኑሮ ቀላል አልሆነላቸውም። አብዛኞቹ በአሠሪዎቻቸው ጉልበታቸው የሚበዘበዝ፣ አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጥቃት የሚፈጸምባቸው፣ በረሃብ የሚሰቃዩ እና ሌሎችም በደሎች ይደርስባቸዋል። ከእነዚህ መካከልም በተለይ ኦማን ውስጥ በሚገኙ አፍሪካውያን የቤት ሠራተኞች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በተመለከተ ቢቢሲ የምርመራ ዘገባ ሠርቷል።
በአንድ ጨዋታ 31 ግቦች የተቆጠሩበት ግብ ጠባቂ
በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ሁሉም ተሰላላፊዎች ለቡድኑ ድል እና ሽንፈት ኃላፊነት ቢኖርባቸውም፣ የግብ ጠባቂን ያህል ግን የጎላ አይሆንም። በተለይ ደግሞ አንድ ቡድን በርካታ ግቦች ተቆጥረውበት ሲሸነፍ የሁሉም ዐይን የሚያርፈው በረኛ ላይ ነው። ታዲያ በአንድ ጨዋታ ከሦስት አስሮች በላይ ጎለረ ያስተናገደ በረኛ ምን ይሰማው ይሆን?
በገዛ ጓደኛዋ ፎቶዋ በረቀቀ ሁኔታ ተቀናብሮ የወሲብ ቪዲዮዎች ድረ-ገጽ ላይ የወጣባት ወጣት
በ20ዎቹ የእድሜዋ አጋማሽ ላይ የምትገኘው ጆዲ ለጠላቷ የማትመኘው ነገር ገጥሟታል። ፎቶግራፏ የእውነት በሚመስል ሁኔታ ተቀነባብሮ ልቅ የወሲብ ፊልሞች በሚታዩባቸው ድረ-ገጾች ላይ ምሥሏ ተሠራጭቶ አግኝታዋለች። ከዚህ እኩይ ተግባር ጀርባ ያለው ደግሞ የቅርቤ የምትለው ጓደኛዋ መሆኑ ጉዳቷን የከፋ አድርጎታል።
የተመለሱ ጥያቄዎች
በመላው ዓለም የሚከበረው የምድር ቀን ምንድን ነው? ምንስ ዓላማ አለው?
የምድር ቀን በመላው ዓለም ሚያዝያ 14/2016 ዓ.ም. (በአውሮፓውያኑ ሚያዝያ 22) በተለያዩ ዝግጅቶች በመላው ዓለም ይታሰባል። ይህ የምድር ቀን ምንድን ነው? ምንስ ዓላማ አለው?
የኢድ አል-ፈጥር በዓል ቀን የሚወሰነው እንዴት ነው?
1445ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል ዛሬ ረቡዕ ሚያዚያ 2/2016 በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ቅዱስ የሆነው የረመዳው ወር ሲጠናቀቅ ከፍ ያለ ሃይማኖታዊ ትርጉም የሚሰጠው የኢድ-አልፈጥር በዓል ይከበራል።
የአእምሮ ጤና እክል የሆነው ባይፖላር ዲስኦርደር ምንድን ነው? ለምንስ ከታዋቂው ሠዓሊ ጋር ተያያዘ?
በተቃራኒ የስሜት ጽንፎች ውስጥ መዋለል (ባይፖላር ዲስኦርደር) ከ100 ሰዎች ውስጥ በአንድ ሰው ላይ ይከሰታል። ስለዚህ የአእምሮ ጤና እክል ግንዛቤን ለማስፋት መጋቢት 21 በየዓመቱ የባይፖላር ዲስኦርደር ቀን ይታሰባል። ይህ ቀን ደግሞ የታዋቂው ሠዓሊ ቪንሰንት ቫን ጎ የልደት ቀን ነው። ዕለቱ ለምን ከእሱ ጋር ተያያዘ? ቫን ጎ ባይፖላር የአእምሮ ጤና ችግር ነበረበት?
የአሜሪካን ገመና ለዓለም ይፋ ያደረገው ጁሊያን አሳንጅ ማን ነው?
የአሜሪካን ገመና ለዓለም ይፋ ያደረገው ዊክሊክስ የተሰኘው ድረ ገጽ መሥራች ጁሊያን አሳንጅ ከሰሞኑ የበርካታ መገናኛ ብዙኃን ዋነኛ ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል።
ችላ ተብለው በአሳሳቢ ደረጃ በመላው ዓለም እየተስፋፉ የመጡት የአባላዘር በሽታዎች
እንደ የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ በመላው ዓለም በየቀኑ ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች በግብረ ሥጋ ግንኙነት በሚተላለፉ በሽታዎች ይያዛሉ። ነገር ግን በትክክል በወሲብ የሚተላለፍ በሽታ ምንድን ነው? ዓይነቶቹ እና ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው? ራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን?
ማንኮራፋት እንዴት ትዳርን እስከ ማፍረስ ሊያደርስ ይችላል? ምንስ መፍትሄ አለው?
የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ለሚያንኮራፋው እና ከጎን ለሚተኛ አካላዊ እና የአእምሮ ጤና ጉዳት ያስከትላል። ትዳር ሊያፈርስ ይችላል።
ፆም በሰውነታችን ውስጥ የሚያስከትለው ለውጥ እና የሚሰጠው ጥቅም ምንድን ነው?
ለእስልምና እና ለክርስትና እመነት ተከታዮች ዋነኞቹ የፆም ወቅት የሆኑት ረመዳን እና ዓቢይ ፆሞች ተጀምረዋል። የሁለቱም እምነቶነቶች ምዕመናን የፆሙን ጊዜ በየራሳቸው ሥርዓት እና ደንብ መሠረት የሚከውኑት ሲሆን፣ በየዕለቱ ለረጅም ሰዓታት ከምግብ እና ከውሃ ርቀው ይቆያሉ። በዚህ ጊዜ ታዲያ ፆም በሰውነት ላይ ምን ለውጥን ያስከትላል? ምንስ ጥቅም አለው?
በረመዳን የፆም ወቅት የትኞቹን ዓይነት ምግቦች መመገብ፣ የትኞቹንስ መተው አለብን?
ረመዳን የፆም ወቅት ሙስሊሞች በጉጉት የሚጠብቁት ጊዜ ነው። ከማለዳ ጀምሮ አስከ ምሽት ድረስ ምግብ ሳይቀመስ የሚቆይበት የፆም ጊዜ የመጀመሪያ ቀናት ለአንዳንዶች ፈታኝ ነው። በፆሙ ወቅት መደበኛ እንቅስቃሴያችንን እያደረግን ያለድካም ለመቆየት የሚያስችሉ ዘዴዎችን የሥነ ምግብ ባለሙያዎች ይመክራሉ። በዚህ ወቅት ምን ዓይነት ምግቦችን መመገብ፤ የትኞችንስ ማስቀረት አለብን?
ራስን ማጥፋት የሚያበረታታው እና ለበርካቶች ሞት ምክንያት የሆነው መርዝ ሻጭ በቢቢሲ ተጋለጠ
በዩናይትድ ኪንግደም ቢያንስ 130 ሰዎች ራሳቸውን አጥፍተውበታል የተባለውን መርዝ የሸጠውን ዩክሬናዊ ቢቢሲ ተከታትሎ ደርሶበታል። ሊዮኒድ ዛኩተንኮ የተባለው ይህ ግለሰብ ራስ ማጥፋትን የሚያበረታታበት እንዲሁም አገልግሎቱን የሚያስተዋውቅበት ድረ ገጽ አለው።
ማር ለጤናችን ምን ያህል ጠቃሚ ነው? መመገብ ያለባቸውስ እነማን ናቸው?
ከስኳር የሚጣፍጠው የተፈጥሮ ማር ብቸኛው የስኳር አማራጭ ነው? ለሁሉም ሰውስ በእኩል ይጠቅማል? ሕጻናትን ለመመገብስ የዕድሜ ገደብ አለው? የምንወስደው መጠንስ ምን ያህል መሆን አለበት? ለእነዚህ የበርካታ ሰዎች የዘውትር ጥያቄዎች የሥነ ምግብ ባለሙያ የሆኑት ጆ ልዊን ምላሽ አላቸው።
የተጠጋገኑ እና ኦሪጂናል ያልሆኑ የሞባይል ቻርጀሮች እኛንም ስልካችንንም እንደሚጎዱ ያውቃሉ?
ሊበጠስ ጫፍ የደረሰ እና የተጠጋገነ የሞባይል ቻርጅ ማድረጊያን መጠቀም ብዙዎቻችን ምንም ጉዳት የሌለው ይመስለናል። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ያልተጠበቀ ሲከፋም አሰቃቂ አደጋን ሊያስከትል ይችላል። በጥሩ ሁኔታ ላይ ያልሆኑ የሞባይል ቻርጀሮችን መጠቀም ምን ችግርን ሊያስከትሉ ይችላሉ? ምን ዓይነት ቻርጀሮችን ብንጠቀም ይመከራል?
ደም ግፊትን ዝቅ ማድረግን ጨምሮ ቀይ ሥር የሚሰጣቸው አምስት ጥቅሞች
የቀይ ሥርን ለየት ያለ ጠቅምን በተመለከተ የሥነ ምግብ እና የጤና ባለሙያዎች መረጃዎችን እያጋሩ ሲሆን፣ በዕለት ከዕለት ምግባችን ውስጥም ቀይ ሥርን እንድናካትት እየመከሩ ነው። ቀይ ሥር የደም ግፊትን እንዴት ሊቀንስ ይችላል? እንዴትስ ነው መመገብ ያለብን?